Skip to main content
news13

የዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል የደም ልገሳ መርሀግብር ማከናወኑን ገለፀ። ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም የዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል ሄኖን ከተሰኘ የበጎ አድራጎት ማህበር፣ በሆስፒታሉ ባለሙያዎች ከተቋቋመዉ Humanitarian & Social Service Unit (HASSU) የበጎ አድራጎት ማህበር እና ከሆሳዕና ደም ባንክ ጋር በመተባበር የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሂዷል። በዛሬዉ ዕለት በሆስፒታሉ በተካሄደው የደም ልገሳ መርሀ-ግብር 29 ዪኒት ደም የተሰበሰበ መሆኑን ታውቋል። በአደጋ እና በተለያዩ ምክንያቶች የደም መፍሰስ ላጋጠማቸው የሆስፒታሉ ታካሚዎችን ህይወት ለማትረፍ የሚረዳ የደም ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ሆስፒታሉ የደም ልገሳ ባህልን ለማሻሻል ከባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ የደም ልገሳና የንቅናቄ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተመላክቷል። በደም ልገሳው መርሀ-ግብሩ ላይ የሆስፒታሉ የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች፣በጎ ፈቃኛ ወጣቶች ፣የሄኖን በጎ አድራጎት ማህበር እና የHASSU አባላት እንዲሁም የዱራሜ ከተማ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተው ደም መለገሳቸው ተገልጿል።